መዝሙር 10:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልቡ፦ “ለልጅ ልጅ አልታወክም ክፉም አያገኘኝም” ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሐሳቡ “የሚያነቃንቀኝ የለም፤ ምንም ችግር ሳያጋጥመኝ ሁልጊዜ እደሰታለሁ” ይላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጥመድ በኃጥኣን ላይ ይዘንባል፤ እሳትና ዲን፥ ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፋንታ ነው። |
አንቺም፣ ‘እስከ መጨረሻው፣ ለዘላለም ንግሥት እሆናለሁ!’ አልሽ፤ ሆኖም እነዚህን ነገሮች አላስተዋልሽም፤ ፍጻሜያቸው ምን እንደሚሆንም አላሰብሽም።
እርስ በርሳቸውም፣ “ኑና የወይን ጠጅ እንገባበዝ፤ እስክንሰክር እንጠጣ፤ ነገም ያው እንደ ዛሬ፣ ምናልባትም የተሻለ ቀን ይሆንልናል” ይባባላሉ።
ለራሷ ክብርና ምቾት የሰጠችውን ያህል፣ ሥቃይና ሐዘን ስጧት፤ በልቧም እንዲህ እያለች ትመካለች፤ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ከቶም አላዝንም፤’