አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
መዝሙር 10:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዐፈር የተፈጠረ ሰው ከእንግዲህ እንዳያስጨንቃቸው፣ አንተ ለድኻ አደጉና ለተገፋው ትሟገታለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርዱ ለወላጅ አልባና ለተጨቆነ ይደረግ ዘንድ፥ ሰዎች በምድር ላይ ማሸበራቸውን እንዳይቀጥሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሌሎችን ለማስፈራራት እንዳይችል፥ አንተ ለወላጅ አልባና ለተጨቈኑ ሰዎች ትከላከላለህ። |
አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤ ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ። ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤ ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤ ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ።
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
“አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፤ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን መልካም ነገሮችን እንደ ተቀበልህ፣ አልዓዛርም ደግሞ ክፉ ነገሮችን እንደ ተቀበለ አስታውስ፤ አሁን ግን እርሱ እዚህ ሲጽናና፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ።