ምሳሌ 9:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴት አገልጋዮቿንም ላከች፤ ከከተማዪቱም ከፍተኛ ቦታ ተጣራች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቶች አገልጋዮችዋን ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገረዶችዋም በከተማው ከፍተኛ ቦታ ላይ ቆመው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮችዋን ልካ በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕድዋ ጠራች። እንዲህም አለች፦ |
ስለዚህም የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ፤ እነርሱ አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤ ሌሎችንም ያሳድዳሉ።’
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ፤ አይሁድ በተሰበሰቡበት ምኵራብ፣ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተምሬአለሁ፤ በስውር የተናገርሁት የለም።