እርሱም ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፣ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።
ምሳሌ 5:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመምህሮቼን ቃል አልሰማሁም፤ አሠልጣኞቼንም አላደመጥኋቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ ጆሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተማሪዎቼ የሚሉትን መስማት አልፈለግሁም፤ ምክራቸውንም አልተቀበልሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፥ ጆሮዎቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም። |
እርሱም ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፣ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።