ምሳሌ 2:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቷ ወደ ሞት ያደርሳል፤ መንገዷም ወደ መናፍስተ ሙታን ያመራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትዋ ወደ ሞት ያዘነበለ ነው፥ አካሄድዋም ወደ ሙታን ጥላ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እርስዋ ቤት ብታመራ ጒዞህ ወደ ሞት ይሆናል፤ ወደ እርስዋ መሄድ ወደ ሙታን ዓለም እንደ መውረድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቷን በሞት አጠገብ አኖረች፥ አካሄድዋንም ከኀያላን ጋር ከምድር ወደ ሲኦል አቀናች። |
ደግሞም ይህን ዕወቁ፤ ማንም አመንዝራ ወይም ርኩስ ወይም ስግብግብ፣ ይኸውም ጣዖት አምላኪ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።
ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”