ምሳሌ 2:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአመንዝራ ሴትም ትጠብቅሃለች፤ በአንደበቷም ከምታታልል ባዕድ ታድንሃለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንግዳይቱ ሴት አንተን ለመታደግ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከማትታወቀው ሴት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እኔ የምልህን ብትሰማ በልዝብ አነጋገር ከምታጠምድ ከአመንዝራ ሴት ማምለጥ ትችላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤ |
ልቧ ወጥመድና አሽክላ፣ እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣ ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤ አምላክን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የዕንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።