ሀብት ብዙ ወዳጅ ታፈራለች፤ ድኻን ግን ወዳጁ ገሸሽ ያደርገዋል።
ባለጠግነት ብዙ ወዳጆች ይጨምራል፥ የድሀ ወዳጅ ግን ከእርሱ ይርቃል።
ሰው በሀብቱ ብዙ ወዳጆችን ያፈራል፤ ድኾችን ግን ያሉአቸው ጥቂት ወዳጆች እንኳ ይከዱአቸዋል።
ባለጠጋ ብዙ ወዳጆችን ይጨምራል፤ ድሃ ግን ያን ያለውን ያጣል።
የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።
ድኾችን ወዳጆቻቸው እንኳ ይጠሏቸዋል፤ ባለጠጎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው።
ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ ውሸት የሚነዛም ሳይቀጣ አይቀርም።