ምሳሌ 18:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤ የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው አፍ ቃል የጠለቀ ውኃ ነው፥ የጥበብም ምንጭ ፈሳሽ ወንዝ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰው አንደበት የሚወጣው የጥበብ ንግግር እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ እንደ ምንጭ ውሃም ጣፋጭ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥ የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው። |
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።