የእስራኤልም ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “መኖሩንማ በርሱ አማካይነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቀው አንድ ነቢይ አሁንም አለ፤ ነገር ግን ምን ጊዜም ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም ትንቢት ተናግሮ ስለማያውቅ እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው” አለ። ኢዮሣፍጥም፣ “ንጉሡ እንዲህ ማለት አይገባውም” አለው።
ምሳሌ 15:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፌዘኛ መታረምን አይወድድም፤ ጠቢባንንም አያማክርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፌዘኛ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ወደ ጠቢባንም አይሄድም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፌዘኛ ተግሣጽን አይወድም፤ ከጠቢባንም ምክርን አይጠይቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላዋቂ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ከጠቢባንም ጋር አይነጋገርም። |
የእስራኤልም ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “መኖሩንማ በርሱ አማካይነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቀው አንድ ነቢይ አሁንም አለ፤ ነገር ግን ምን ጊዜም ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም ትንቢት ተናግሮ ስለማያውቅ እጠላዋለሁ፤ እርሱም የይምላ ልጅ ሚክያስ ነው” አለ። ኢዮሣፍጥም፣ “ንጉሡ እንዲህ ማለት አይገባውም” አለው።
“እናንተ አላዋቂዎች፤ ማስተዋል የሌለበት መንገዳችሁን እስከ መቼ ትወድዱታላችሁ? ፌዘኞች በፌዝ ደስ የሚሰኙት፣ ሞኞችስ ዕውቀትን የሚጠሉት እስከ መቼ ነው?
ምክንያቱም ሰዎች ትክክለኛ የሆነውን ትምህርት የማይቀበሉበት ጊዜ ይመጣል፤ ከዚህ ይልቅ ለገዛ ምኞቶቻቸው የሚስማማውን፣ የሚያሳክክ ጆሯቸው ሊሰማ የሚፈልገውን እንዲነግሯቸው በዙሪያቸው ብዙ አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ።