ምሳሌ 10:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፥ የክፉ ልብ ግን ዋጋ ቢስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደግ ሰው ንግግር እንደ ነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው አሳብ ግን ዋጋቢስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፤ የኃጥኣን ልብ ግን ይጐድላል። |
እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም።