ምሳሌ 1:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የጠቢባንን ምሳሌዎችና ተምሳሌቶች፣ አባባሎችና ዕንቈቅልሾች ይረዱ ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሳሌንና ምሥጢርን የጠቢባንን ቃልና ዕንቆቅልሸ ለማስተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ስውር የሆኑ የምሳሌዎችን ምሥጢር ጠቢባን የሚያቀርቡአቸውን እንቆቅልሾች መረዳት ያስችላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቈቅልሾችን ያውቃል። |
የጠቢባን ቃላት እንደ ሹል የከብት መንጃ ናቸው፤ የተሰበሰቡ አባባሎቹም እጅግ ተቀብቅበው እንደ ገቡ ችንካሮች ሲሆኑ፣ ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው።
እኔ ከርሱ ጋራ የምነጋገረው ፊት ለፊት ነው፤ በግልጽ እንጂ በልዩ ዘይቤ አይደለም፤ እርሱ የእግዚአብሔርን መልክ ያያል። ታዲያ እናንተ አገልጋዬን ሙሴን ትቃወሙ ዘንድ ለምን አልፈራችሁም?”
እርሱ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፏል፤ በመልእክቶቹም ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ፣ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።