ጽድቅን፣ ፍትሕንና ሚዛናዊ ብያኔን በማድረግ፣ የተገራ ጠቢብ ልቡናን ለማግኘት፤
የጥበብን ትምህርት ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንም ለመቀበል፥
እነርሱም እውነትን ፍትሕንና ቅንነትን በመከተል ሥርዓትንና ጥበብን ወደ ተሞላ ሕይወት ይመራሉ።
የቃልን መልስ ለመቀበል በእውነት ጽድቅንም ለማወቅ ፍርድንም ለማቃናት፥
እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ የሰጠውን ፍርድ ሲሰሙ ፈሩት፤ ፍትሕ ለመስጠት የአምላክን ጥበብ የታደለ መሆኑን አይተዋልና።
ምክርን ከአፉ ተቀበል፤ ቃሉንም በልብህ አኑር።
ምክርን ስማ፤ ተግሣጽን ተቀበል፤ በመጨረሻም ጠቢብ ትሆናለህ።
ለላከህ ተገቢውን መልስ ትሰጥ ዘንድ፣ እውነተኛና የታመኑ ቃሎችን እንዳስተምርህ አይደለምን?
ሰባኪው ትክክለኛውን ቃል ለማግኘት ተመራመረ፤ የጻፈውም ቅንና እውነት ነበረ።