ምሳሌ 1:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክሬን ሁሉ ስለ ናቃችሁ፣ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክሬን ሁሉ ግን ችላ ስላላችሁ፥ ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምክሬን ናቃችሁ፤ ተግሣጼንም አልተቀበላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምክሬን ሁሉ ናቃችሁ፥ ዘለፋዬንም አልተመለከታችሁም፥ |
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሣሣና ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሣለቁ፤ ቃሉን ናቁ፤ ነቢያቱንም አቃለሉ።
“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አደርሳለሁ ያልሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ፤ በተናገርኋቸው ጊዜ፣ አልሰሙኝምና በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝም።’ ”