ምሳሌ 1:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ በጐዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፤ በየአደባባዩ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች፥ በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ በመንገድ ላይ ትጮኻለች፤ በአደባባይም ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ታሰማለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብ በጎዳና ትመሰገናለች፤ በአደባባይም ድምፅዋን ትሰጣለች። |
ወደ ገዛ አገሩ መጣ፤ በምኵራባቸውም ሕዝቡን ያስተምር ጀመር። እነርሱም በመገረም እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና እነዚህን ታምራት የማድረግ ኀይል ከየት አገኘ?
ስለዚህም የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ፤ እነርሱ አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤ ሌሎችንም ያሳድዳሉ።’