ምሳሌ 1:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ ዕሺ አትበላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! ኃጢአተኞች እንድትከተላቸው ቢያባብሉህ እሺ አትበላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ዝንጉዎች ሰዎች አያስቱህ፤ እሽም አትበላቸው። |
በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣
እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ሆድ ነው። በለሰለሰ አንደበታቸውና በሽንገላ የዋሆችን ያታልላሉ።