ዘኍል 8:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹ በመቅረዙ ላይ ሆነው ፊት ለፊት እንዲያበሩ አስቀመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አሮንም እንዲህ አደረገ፤ በመቅረዙ ፊት ለፊት እንዲበሩ በማድረግም መብራቶቹን አኖረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን አበራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። |
“አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም በለው፤ ‘ሰባቱን መብራቶች በየቦታቸው በምታስቀምጥበት ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ላለው አካባቢ ብርሃን ይሰጣሉ።’ ”
የመቅረዙ አሠራር እንዲህ ነበር፤ ከመቆሚያው እስከ አበቦቹ ያለው ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የመቅረዙም አሠራር እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው መሠረት ነበር።