ዘኍል 7:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በመገናኛውም ድንኳን ለአገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ከእነርሱ ተቀበል፤ ለእያንዳንዳቸውም ለአገልግሎታቸው በሚያስፈልጋቸው መጠን ለሌዋውያኑ ስጣቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለመገናኛው ድንኳን መገልገያ እንዲሆኑ እነዚህን ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገልግሎታቸው ትሰጣቸዋለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚከናወነው ተግባር መገልገያ ይሆኑ ዘንድ እነዚህን መባዎች ተቀበል፤ ለእያንዳንዳቸው አገልግሎት በሚያስፈልጋቸው መጠን መድበህ ለሌዋውያን ስጣቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለምስክሩ ድንኳን ሥራ የሚያገለግል ይሆን ዘንድ፥ ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገልግሎታቸው ስጣቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመገናኛው ድንኳን ማገልገል ይሆን ዘንድ ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገግሎታቸው ስጣቸው። |
ይህም የታመነ ቃል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑቱ መልካሙን ነገር ለማድረግ ራሳቸውን አሳልፈው ይሰጡ ዘንድ እነዚህን ነገሮች አስረግጠህ እንድትናገር እፈልጋለሁ። ይህ መልካምና ለማንኛውም ሰው የሚጠቅም ነው።