እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፏቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።
ዘኍል 32:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንዲሸነፍ ያደረገው ይህ ሁሉ ምድር ለከብት ምቹ ነው፤ እኛ አገልጋዮችህም ከብቶች አሉን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የእስራኤል ማኅበር እንዲወርሰው ያደረገው ምድር ሲሆን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባርያዎችህ እንስሶች አሉን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆች ፊት የሰጣት ምድር የከብት መሰማሪያ ሀገር ናት፤ ለእኛም ለአገልጋዮችህ ብዙ እንስሳት አሉን። |
እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ወደዚህ ቦታ የመጡት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈጽመው አጠፏቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ የግጦሽ ቦታ ስላገኙም፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።
ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣ በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣ የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን፣ በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
እስራኤል ግን በሰይፍ መታው፤ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ድረስ ያለውንም ምድሩን ወሰደበት፤ ይሁን እንጂ የአሞናውያን ወሰን የተመሸገ ስለ ነበር ከያቦቅ አላለፈም።
እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እርሱን ከመላው ሰራዊቱና ከምድሩ ጋራ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን ሁሉ በርሱም ላይ አድርግበት” አለው።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ከፊትህ በማስወጣት ወደ ምድራቸው አስገብቶህ ለአንተ ርስት አድርጎ ለመስጠት ነው።