ዘኍል 23:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ያልረገመውን፣ እኔ እንዴት ረግማለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ፣ እንዴት አወግዛለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? ጌታስ ያላወገዘውን እንዴት አወግዛለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እኔ እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግመዋለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ እንዴት አወግዛለሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ? |
ስለዚህ ይህን ሕዝብ መቋቋም ስለማልችል መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባትም ድል አድርጌ ከአገሪቱ ላስወጣቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል፤ አንተ የምትባርከው ቡሩክ፣ የምትረግመውም ርጉም እንደሚሆን ዐውቃለሁና።”
በያዕቆብ ላይ የሚሠራ አስማት የለም፤ በእስራኤልም ላይ የሚሠራ ሟርት አይኖርም፤ ለያዕቆብና ለእስራኤል፣ ‘እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ!’ ይባልላቸዋል።
ከዚያም በለዓም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፣ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች። ‘ና ያዕቆብን ርገምልኝ፤ መጥተህም እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ።