ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።
ዘኍል 18:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌዋውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ምርጥ የሆነውን ክፍል በምታቀርቡበት ጊዜ፣ እንደ ዐውድማ ምርት ወይም እንደ ወይን መጭመቂያ ውጤት ሆኖ ይቈጠርላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እነርሱን እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘ከእርሱ የተመረጠውን ባቀረባችሁ ጊዜ ከአውድማው እህልና ከወይን መጭመቂያው እንደ ተገኘ ምርት ለሌዋውያን ይቈጠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምርጥ የሆነውን ነገር በምትሰጡበት ጊዜ ገበሬ መባውን ከሰጠ በኋላ የተረፈውን ለራሱ እንደሚያስቀር እናንተም የተረፈውን ለራሳችሁ ታስቀራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ትላቸዋለህ፦ ከእርሱ ከመጀመሪያው በለያችሁ ጊዜ እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ለሌዋውያን ይቈጠርላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ትላቸዋለህ፦ ከእርሱ የተመረጠውን ባነሣችሁ ጊዜ እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ለሌዋውያን ይቈጠራል። |
ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።
እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።
የታወረውን እንስሳ ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፣ ያ በደል አይደለምን? ዐንካሳውን ወይም በሽተኛውን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ያስ በደል አይደለምን? ያንኑ ለገዣችሁ ብታቀርቡ፣ በእናንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ይቀበለዋልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የቀረው ግን በመገናኛው ድንኳን ለሰጣችሁት አገልግሎት ደመወዛችሁ ስለ ሆነ፣ እናንተና ቤተ ሰዎቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ልትበሉት ትችላላችሁ።