ዘኍል 18:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤላውያን የመከር በኵራት አድርገው ለእግዚአብሔር የሚሰጡትን ምርጥ የወይራ ዘይት በሙሉ፣ ምርጥ የሆነውን አዲስ የወይን ጠጅና እህል ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከእህልም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላውያን የሚሰጡኝን ምርጥ የሆነ በኲራት፥ ይኸውም የወይራ ዘይት፥ የወይን ጠጅና እህል ለእናንተ እሰጣችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከስንዴም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከእህልም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ። |
አንድ ሰው ከበኵራቱ ፍሬ የተጋገረ ሃያ የገብስ ሙልሙልና ጥቂት የእሸት ዛላዎች በአቍማዳ ይዞ ከበኣልሻሊሻ ወደ እግዚአብሔር ሰው መጣ። ኤልሳዕም አገልጋዩን፣ “ሰዎቹ እንዲበሉት ስጣቸው” አለው።
ትእዛዙ እንደ ወጣ እስራኤላውያን ወዲያውኑ የእህሉንና የአዲሱን ወይን ጠጅ፣ የዘይቱንና የማሩን እንዲሁም የዕርሻውን ፍሬ ሁሉ በኵራት በልግስና ሰጡ፤ ካላቸው ከማንኛውም ነገር ሁሉ ላይ እጅግ ብዙ የሆነ ዐሥራት አውጥተው አመጡ።
ከፍሬ በኵራት ምርጥ የሆነው ሁሉ እንዲሁም ከልዩ ስጦታዎቻችሁ የመጀመሪያው ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ ለቤተ ሰዎቻችሁ ሁሉ በረከት እንዲሆን ከምድር የምታገኙትን መብል በኵራት ለእነርሱ ስጧቸው።
እነዚህን የበኵራት ቍርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ሽታው ደስ የሚያሰኝ ቍርባን ሆነው በመሠዊያ ላይ ለመቃጠል አይቀርቡም።
በሁለት ዐሥረኛ የኢፍ መስፈሪያ የላመ ዱቄት፣ በእርሾ የተጋገረ ሁለት እንጀራ ለሚወዘወዝ መሥዋዕት፣ የበኵራት ስጦታ እንዲሆን ከየቤታችሁ ለእግዚአብሔር አምጡ።
ካህኑም ሁለቱን የበግ ጠቦቶች ከበኵራቱ እንጀራ ጋራ የሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ እነዚህም ለእግዚአብሔር ቅዱስ መሥዋዕት፣ የካህኑም ድርሻ ናቸው።
አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል ሁሉ፣ በኵራት ወስደህ በቅርጫት ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም አምላክህ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ፤
የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወተት፣ የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፣ የባሳንን ምርጥ አውራ በግ፣ መልካም የሆነውንም ስንዴ፣ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ።