ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የእናንተ ድርሻ ሆኖ ስለ ተሰጠ፣ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ በሆነ ስፍራ ብሉት።
ዘኍል 18:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤላውያን ከሚያቀርቡት ስጦታ፣ ከሚወዘወዘው ቍርባን ተለይቶ የሚቀመጠው ስጦታ ሁሉ የአንተ ይሁን። ይህንም ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። ከቤተ ሰዎችህ በሥርዐቱ መሠረት የነጻ ማንኛውም ሰው ከዚሁ መብላት ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ደግሞ ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ የሚያቀርቡትን የመወዝወዝ ቁርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በተጨማሪም እስራኤላውያን በእኔ ፊት በመወዝወዝ የሚያቀርቡአቸው ልዩ ስጦታዎች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ እነርሱን ለአንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤ ንጹሕ የሆነ ማንኛውም የቤተሰብህ አባል ሊመገባቸው ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ለእናንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀደሰ ይሆንልሃል። ይህም ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የማንሣትና የመወዝወዝ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። |
ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የእናንተ ድርሻ ሆኖ ስለ ተሰጠ፣ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ በሆነ ስፍራ ብሉት።
ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ።
እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፤ “መቅደሱን በተመለከተ ስለሚፈጸም በደል አንተ፣ ልጆችህና የአባትህ ቤተ ሰቦች ኀላፊነቱን ትሸከማላችሁ፤ ክህነቱን በተመለከተ ስለሚፈጸም በደል ግን ኀላፊነቱ የሚወድቀው በአንተና በልጆችህ ላይ ብቻ ነው።
እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ከተቀደሰ ቍርባን የሚለየው ሁሉ ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም በእግዚአብሔር ፊት ለአንተና ለዘሮችህ ዘላለማዊ የጨው ኪዳን ነው።”
ከዚያም እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፤ “ለእኔ በሚቀርበው መባ ላይ ኀላፊነትን የሰጠሁህ እኔው ራሴ ነኝ፤ እስራኤላውያን የሚያቀርቡልኝም የተቀደሰ መባ ሁሉ ለአንተና ለልጆችህ መደበኛ ድርሻችሁ እንዲሆን ሰጥቻችኋለሁ።