ዐማቱም ሙሴ ለሕዝቡ የሚያደርገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከጧት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመው ሳለ፣ ብቻህን በፍርድ ወንበር ላይ ለምን ትቀመጣለህ?” አለው።
ዘኍል 15:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰውየው ላይ ምን መደረግ እንዳለበት ግልጽ የሆነ ነገር ባለመኖሩ በጥበቃ ሥር እንዲቈይ አደረጉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም ላይ ምን ሊደረግበት እንደሚገባ ገና ግልጽ አልነበረምና በእስር ቤት አኖሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ግልጥ ሆኖ ስላልተገኘ ለጊዜው በዘብ ተጠብቆ እንዲቈይ ተደረገ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴት እንደሚያደርጉት አልፈረዱምና በግዞት ቤት አዋሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያደርጉበትም ዘንድ የሚገባው አልተገለጠምና በግዞት አስቀመጡት። |
ዐማቱም ሙሴ ለሕዝቡ የሚያደርገውን ሁሉ ባየ ጊዜ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከጧት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመው ሳለ፣ ብቻህን በፍርድ ወንበር ላይ ለምን ትቀመጣለህ?” አለው።