ዐሥራቱን በሚቀበሉበት ጊዜም ከአሮን ዘር የተወለደው ካህን ከሌዋውያኑ ጋራ ዐብሮ ይገኛል፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን አንድ ዐሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደ ዕቃ ማከማቻ ክፍሎች ያመጡታል።
ዘኍል 15:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድሪቱን በረከት ስትመገቡ ከዚሁ ላይ አንሥታችሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለጌታ እንደ ልዩ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምድሪቱ የሚመረተውን ነገር ሁሉ በምትመገቡበት ወቅት ከእርሱ ላይ ጥቂት በማንሣት ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጋችሁ አቅርቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደማመጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን ታደርጋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን ታደርጋላችሁ። |
ዐሥራቱን በሚቀበሉበት ጊዜም ከአሮን ዘር የተወለደው ካህን ከሌዋውያኑ ጋራ ዐብሮ ይገኛል፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን አንድ ዐሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደ ዕቃ ማከማቻ ክፍሎች ያመጡታል።