La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 10:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሰፈራቸው በሚነሡበት ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀን ቀን ከላያቸው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሰፈራቸውም በተጓዙ ጊዜ የጌታ ደመና ቀን ቀን በእነርሱ ላይ ነበረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእያንዳንዱ ሰፈር ሲለቁ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ይጋርዳቸው ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም ታቦቷ በተ​ጓ​ዘች ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ተነሣ፤ ጠላ​ቶ​ችህ ይበ​ተኑ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ህም ከፊ​ትህ ይሽሹ” ይል ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሰፈራቸውም በተጓዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀን ቀን በላያቸው ነበረ።

Ver Capítulo



ዘኍል 10:34
7 Referencias Cruzadas  

ቀን በደመና ዐምድ፣ በሚሄዱበት መንገድ ታበራላቸውም ዘንድ ሌሊት በእሳት ዐምድ መራሃቸው።


“ከርኅራኄህ ብዛት የተነሣ በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፤ ቀን የደመናው ዐምድ በመንገዳቸው ላይ መምራቱን፣ ሌሊትም የእሳቱ ዐምድ በሚሄዱበት ላይ ማብራቱን አላቆመም።


ደመናን እንደ መጋረጃ ዘረጋላቸው፤ እሳትም በሌሊት አበራላቸው።


ስለዚህ በጕዟቸው ሁሉ ወቅት፣ በእስራኤል ቤት ፊት ሁሉ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ከማደሪያው በላይ፣ በሌሊትም እሳቱ በደመናው ውስጥ ነበር።


ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር።