ማቴዎስ 5:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በራስህም ቢሆን አትማል፤ ከጠጕራችሁ መካከል አንዲቷን እንኳ ነጭ ወይም ጥቍር ማድረግ አትችሉምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በራስህም አትማል፤ አንዲቱን ጠጉር እንኳ ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጸጒርህ አንዲቱን እንኳ ነጭ ወይም ጥቊር ማድረግ ስለማትችል በራስህም ቢሆን አትማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራስህም አትማል፤ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። |
ስለዚህ ስትነጋገሩ ቃላችሁ፣ ‘አዎን’ ከሆነ ‘አዎን’፤ ‘አይደለም’ ከሆነ ‘አይደለም’ ይሁን፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ሁሉ ከክፉው የሚመጣ ነውና።