ማቴዎስ 5:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድርም ቢሆን አትማሉ፤ የእግዚአብሔር የእግሩ ማረፊያ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አትማሉ፤ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርም አትማሉ የእግሩ ማረፊያ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አትማሉ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድርም የጌታ እግር ማሳረፊያ ስለ ሆነች በምድርም አትማሉ፤ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ስለ ሆነች በኢየሩሳሌምም አትማሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ቤት የት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?
“በመንጋው ውስጥ ተቀባይነት ያለው ተባዕት በግ ኖሮት ይህንኑ ሊሰጥ ተስሎ ሳለ፣ በማታለል ነውር ያለበትን እንስሳ ለጌታ የሚሠዋ ርጉም ይሁን፤ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ ሊፈራ የሚገባ ነውና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?