ማቴዎስ 25:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሽራው በዘገየ ጊዜ፣ ሁሉም እንቅልፍ ተጫጫናቸውና ተኙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ፥ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሽራው በመዘግየቱ ሁሉም እንቅልፍ ተጫጭኖአቸው ተኙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ፥ ሁሉም እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። |
እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።”
ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃልና፤ ስለ መጨረሻውም ይናገራል፤ እርሱም አይዋሽም፤ የሚዘገይ ቢመስልም ጠብቀው፤ በርግጥ ይመጣል፤ ከቶም አይዘገይም።
ከዚያም ተመልሶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመጣ፣ ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ፤ ከእኔ ጋራ ለአንድ ሰዓት እንኳ መትጋት አቃታችሁን?
ነገር ግን ያ ባሪያ፣ ‘ጌታዬ ቶሎ አይመጣም፤ ይዘገያል’ ብሎ ቢያስብና ወንድና ሴት ብላቴኖችን ቢደበድብ፣ ደግሞም እንዳሻው ቢበላና ቢጠጣ መስከር ቢጀምር፣
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ለሕዝቡ ይነግራቸው ጀመር፤ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ለገበሬዎችም አከራየና ወደ ሌላ አገር ሄዶ ብዙ ጊዜ ቈየ።
ዘመኑን በማስተዋል ይህን አድርጉ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ጊዜ አሁን ነው፤ መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን ወደ እኛ ቀርቧልና።
ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።