ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የወርካ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጕቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጕቶ ሆኖ ይቀራል።”
ማቴዎስ 24:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቀኖቹ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ባልተረፈ ነበረ፤ ስለ ተመረጡት ሲባል ግን እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያ ቀኖች ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ተመረጡት ሰዎች እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ ቀኖች ባያጥሩማ ኖሮ አንድም ሰው መዳን ባልቻለ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ተመረጡት ሰዎች እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ። |
ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የወርካ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጕቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጕቶ ሆኖ ይቀራል።”
ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዪቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማዪቱ እኩሌታ ይማረካል፤ የሚቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዪቱ አይወሰድም።
እርሱም መላእክቱን ከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋራ ይልካቸዋል፤ እነርሱም ምርጦቹን ከአራቱ ነፋሳት፣ ከሰማያት ከአንዱ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ይሰበስባሉ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፤ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በእስያና በቢታንያ ተበትነው በመጻተኛነት ለሚኖሩ ለእግዚአብሔር ምርጦች፤