“ ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ ያልሁትን ክፉ ነገር እንደሚፈጸም ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሁናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር።
ማቴዎስ 24:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተነገረው፣ ‘የጥፋት ርኩሰት’ በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፣ አንባቢው ያስተውል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ባያችሁ ጊዜ አንባቢው ያስተውል! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ |
“ ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ ያልሁትን ክፉ ነገር እንደሚፈጸም ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሁናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር።
ሰውየውም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በዐይንህ እይ፤ በጆሮህ ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፤ ወደዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና ያየኸውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።”
“የጦር ሰራዊቱም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ።
አንተ እጅግ የተወደድህ ስለ ሆንህ፣ ገና ልመናህን ስትጀምር መልስ ተሰጥቷል፤ እኔም ይህን ልነግርህ መጣሁ። ስለዚህ መልእክቱን ልብ በል፤ ራእዩንም አስተውል።
“ይህን ዕወቅ፤ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ፣ ገዥው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ፣ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል። ኢየሩሳሌም ከጐዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋራ ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው።
አለቃው ከብዙዎች ጋራ ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕትና ቍርባን ማቅረብን ያስቀራል። የታወጀው ፍርድ በርሱ ላይ እስኪፈስስ ድረስ፣ ጥፋትን የሚያመጣ የጥፋት ርኩሰት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያቆማል።”
እንዲህም እያሉ ጮኹ፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ርዱን! ሕዝባችንንና ሕጋችንን እንዲሁም ይህን ስፍራ በማጥላላት በደረሰበት ስፍራ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ የሚያስተምረው ሰው ይህ ነው፤ ከዚህም በላይ ግሪኮችን ወደ ቤተ መቅደስ እያስገባ ይህን የተቀደሰ ስፍራ የሚያረክሰው እርሱ ነው።”
እንዲህ ብለው የሚመሰክሩ የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ “ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራና በሕጉ ላይ የስድብ ቃል መናገሩን በፍጹም አልተወም፤