ማቴዎስ 22:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱም አንድ የኦሪት ሕግ ዐዋቂ፣ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም አንድ የሕግ መምህር፥ ኢየሱስን ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው፦ |
“እናንተ ሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ! የዕውቀትን መክፈቻ ነጥቃችሁ ወስዳችኋልና፤ እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ የሚገቡትንም ከልክላችኋል።”
ይህን ጥያቄ ያቀረቡለት፣ እርሱን የሚከስሱበት ምክንያት ለማግኘት ሲፈትኑት ነው። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ይጽፍ ጀመር።