ማቴዎስ 22:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያው ቀን፣ ትንሣኤ የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን የሙታን ትንሣኤ የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ቀን፥ “የሙታን ትንሣኤ የለም” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ቀን “ትንሣኤ ሙታን የለም፤” የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ቀረቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ቀን፦ ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ ቀረቡ፥ |
ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የእፉኝት ልጆች! ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ?