La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 21:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህ የሆነውም በነቢዩ እንዲህ በማለት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህም በነቢዩ እንዲህ የብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፦

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህም የሆነው በነቢይ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፦

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለጽዮን ልጅ ‘እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፤’ በሉአት።” ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለጽዮን ልጅ፦ እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 21:4
9 Referencias Cruzadas  

አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።


ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤


ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልጋሉ፤ እርሱም ወዲያውኑ መልሶ ይልካቸዋል’ በሉት።”


ነገር ግን ይህ ሁሉ የሆነው ነቢያት በቅዱሳት መጻሕፍት የተናገሩት ይፈጸም ዘንድ ነው።” በዚያ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።


ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሶቻቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት።


ከዚያም ውርንጫውን ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሶቻቸውን በላዩ ጣል አድርገው ኢየሱስን በውርንጫው ላይ አስቀመጡት።


በማግስቱም ለበዓሉ የመጣው ብዙ ሕዝብ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየመጣ መሆኑን ሰሙ፤


“የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አትፍሪ፤ እነሆ፤ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣል።”