ከከርቤና ከዕጣን፣ ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣ መዐዛዋ የሚያውድ፣ እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትወጣው ይህች ማን ናት?
ማቴዎስ 21:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም ከተማዋ በመላ፣ “ይህ ማነው?” በማለት ታወከች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ “ይህ ማን ነው?” ብሎ መላው ከተማ ተናወጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ የከተማው ሰዎች በሙሉ “ይህ ማን ነው?” በማለት ታወኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ “ይህ ማን ነው?” ብሎ ተናወጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ፦ ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ። |
ከከርቤና ከዕጣን፣ ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣ መዐዛዋ የሚያውድ፣ እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትወጣው ይህች ማን ናት?
ይህ ከኤዶም፣ ቀይ የተነከረ መጐናጸፊያ ለብሶ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው? ይህ ክብርን የተጐናጸፈ፣ በኀይሉ ታላቅነት እየተራመደ የሚመጣውስ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ ለማዳንም ኀይል ያለኝ እኔው ነኝ።”
ቀድሞት የሚሄደውና ይከተለው የነበረው ሕዝብም እንዲህ እያለ ይጮኽ ነበር፤ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ!” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!” “ሆሳዕና በአርያም!”
ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም፣ “አምላክን በመሳደብ እንዲህ የሚናገር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።
ሄሮድስም፣ “መጥምቁ ዮሐንስን እኔው ራሴ ዐንገቱን አስቈርጬው ሞቷል፤ ታዲያ፣ ስለ እርሱ እንዲህ ሲወራ የምሰማው ይህ ሰው ማነው?” አለ፤ በዐይኑም ሊያየው ይሻ ነበር።
ከዚያም ሁለቱ ሴቶች እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ተጓዙ፤ ቤተ ልሔም እንደ ደረሱም፣ በእነርሱ ምክንያት ከተማው በሙሉ ተተረማመሰ፤ ሴቶቹም፣ “ይህች ኑኃሚን ናትን?” በማለት ተገረሙ።
ሳሙኤል እግዚአብሔር ያለውን ነገር አደረገ። ቤተ ልሔም እንደ ደረሰም፣ የከተማዪቱ ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡ፣ እነርሱም “አመጣጥህ ለሰላም ነውን?” ብለው ጠየቁት።