ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።
ማቴዎስ 18:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወንድምህ ቢበድልህ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁ ጥፋቱን ንገረው። ቢሰማህ፣ ወንድምህን እንደ ገና የራስህ ታደርገዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወንድምህ ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ገሥጸው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ታተርፈዋለህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወንድምህ ቢበድልህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ በደሉን ንገረው፤ ቢሰማህ እንደገና ወንድምህ እንዲሆን ታደርገዋለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ |
ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።
እንግዲህ እኔ የጻፍሁላችሁ ስለ በደለው ወይም ስለ ተበደለው ሰው አይደለም፤ ነገር ግን ለእኛ ምን ያህል ታማኞች እንደ ሆናችሁ፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን እንድታዩ በማለት ነው።
ወንድሞች ሆይ፤ አንድ ሰው በኀጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል። ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ።
በዚህም ነገር ማንም ተላልፎ ወንድሙን አያታልል፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ እንደ እነዚህ ያለውን ኀጢአት ሁሉ የሚፈጽሙትን ይበቀላል፤