ማቴዎስ 15:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደቀ መዛሙርትህ የአባቶችን ወግ የሚተላለፉት ለምንድን ነው? ምግብ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ደቀ መዛሙርትህ ለምን የሽማግሌዎችን ልማድ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ ስለምን ያፈርሳሉ? እነሆ! ምግብ የሚበሉት እጃቸውን ሳይታጠቡ ነው!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና፤” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና አሉት። |
በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ወግና በዚህ ዓለም መሠረታዊ መንፈሳዊ ኀይሎች ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።