ማቴዎስ 15:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው፣ “ፈሪሳውያን ያልኸውን ሰምተው እንደ ተቈጡ ዐወቅህ?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ቀርበው “ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ ታውቃለህን?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፦ “ፈሪሳውያን ይህን የተናገርከውን ሰምተው እንደ ተሰናከሉ ዐውቀሃልን?” ሲሉ ጠየቁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው “ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው፦ ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን? አሉት። |
ሆኖም እንዳናስቀይማቸው ሄደህ መንጠቈህን ወደ ባሕር ጣል፤ መጀመሪያ የምትይዘውን ዓሣ አፉን ስትከፍት የምታገኘውን አንድ እስታቴር በእኔና በአንተ ስም ክፈል።”
ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ሰላም ወዳድ፣ ታጋሽ፣ ዕሺ ባይ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፣ አድልዎና ግብዝነት የሌለባት ናት።