ማቴዎስ 15:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና እንዲህ አሉት፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ፥ ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ወደ ኢየሱስ ቀርበው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና፦ |
አንድ ቀን ኢየሱስ እያስተማረ ነበር፤ በዚያም ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮች ሁሉ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ተቀምጠው ነበር፤ ይፈውስም ዘንድ የጌታ ኀይል ከርሱ ጋራ ነበረ።
ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም፣ “አምላክን በመሳደብ እንዲህ የሚናገር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።
ፈሪሳውያንና ጸሐፍታቸውም “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ‘ከኀጢአተኞች’ ጋራ የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” እያሉ በደቀ መዛሙርቱ ላይ አጕረመረሙ።
ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የኦሪት ሕግ መምህራንም ተነሥተው፣ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮትስ እንደ ሆነ ምን ይታወቃል?” በማለት አጥብቀው ተከራከሩ።