ማቴዎስ 13:56 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኅቶቹስ ከእኛው ጋራ አይደሉምን? ታዲያ ይህ ሰው ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅቶቹስ ሁሉ ከእኛ ጋር ያሉ አይደሉምን? ታዲያ ይህን ሁሉ ከየት አገኘው?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኅቶቹስ ሁሉ ከእኛ ጋር አይደሉምን? ታዲያ፥ ይህ ሰው ይህን ሁሉ ጥበብ ከየት አገኘው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው?” ተሰናከሉበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም። |
ይህ ዐናጺው አይደለምን? የማርያም ልጅ፣ የያዕቆብ፣ የዮሴፍ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚሁ እኛው ዘንድ አይደሉምን?” ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት።