ማቴዎስ 13:55 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ የዐናጺው ልጅ አይደለምን? የእናቱስ ስም ማርያም አይደለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ የጠራቢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፥ ዮሴፍ፥ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ የአናጢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም የምትባል አይደለችምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብ፥ ዮሴፍ፥ ስምዖንና ይሁዳ አይደሉምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ፥ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? |
እግዚአብሔር፣ ታዳጊ የሆነው የእስራኤል ቅዱስ፣ ለተናቀውና በሕዝብ ለተጠላው፣ የገዦች አገልጋይ እንዲህ ይላል፤ “ነገሥታት አይተውህ ይነሣሉ፤ ልዑላንም አይተው ይሰግዳሉ፤ ምክንያቱም የመረጠህ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ነው።”
በዚህ ጊዜ ሴቶች ከሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፣ የታናሹ ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፣ እንዲሁም ሰሎሜ ነበሩ፤
ይህ ዐናጺው አይደለምን? የማርያም ልጅ፣ የያዕቆብ፣ የዮሴፍ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚሁ እኛው ዘንድ አይደሉምን?” ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት።