ማቴዎስ 12:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይጨቃጨቅም ወይም አይጮኽም፤ ድምፁም በአደባባይ አይሰማም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይከራከርም አይጮህምም፤ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አይከራከርም ወይም አይጮኽም፤ በመንገዶችም ላይ ድምፁን የሚሰማ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይከራከርም፤ አይጮህምም፤ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። |
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
ፈሪሳውያን የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ እንደምትመጣ ኢየሱስን በጠየቁት ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት በሚታዩ ምልክቶች አትመጣም፤
እኔ ጳውሎስ፣ በእናንተ ፊት ስሆን “ዐይነ ዐፋር”፣ ከእናንተ ስርቅ ግን፣ “ደፋር” የተባልሁ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እለምናችኋለሁ።