ማቴዎስ 12:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሆነው በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው። |
የባሪያዎቼን ቃል እፈጽማለሁ፤ የመልእክተኞቼን ምክር አጸናለሁ። “ኢየሩሳሌምን ‘የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፣’ የይሁዳ ከተሞችንም፣ ‘ይታነጻሉ’፣ ፍርስራሻቸውን፣ ‘አድሳለሁ’ እላለሁ።
እርሱም፣ “ከእናንተ ጋራ በነበርሁበት ጊዜ፣ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል’ ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው” አላቸው።