ማቴዎስ 11:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ከሄዱ በኋላ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ወደ ምድረ በዳ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ሸንበቆ በነፋስ ሲወዛወዝ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ “ወደ ምድረ በዳ ምን ልታዩ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸምበቆ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ፥ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤ “ለመሆኑ ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ “ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ፦ ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? |
የዮሐንስ ጥምቀት የመጣው ከየት ነበር? ከሰማይ ወይስ ከሰው?” እነርሱም እርስ በርስ በመነጋገር እንዲህ ተባባሉ፤ “ ‘ከሰማይ ነው?’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤
ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉት አየና፣ “ምን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ረቢ፣ የት ትኖራለህ?” አሉት፤ “ረቢ” ማለት መምህር ማለት ነው።
ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም።