እኔ በጥንቃቄ አደመጥኋቸው፤ ትክክለኛ የሆነውን ግን አይናገሩም። ማንም ስለ ክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ “ምን አድርጌአለሁ?” ይላል። ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ፈረስ፣ እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይሄዳል።
ማቴዎስ 11:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢየሱስ ብዙውን ታምራት ያደረገባቸው ከተሞች ንስሓ ባለመግባታቸው እንዲህ ሲል ወቀሳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ብዙ ተአምራት ያደረገባቸውን ከተሞች ንስሓ ስላልገቡ ይነቅፋቸው ጀመር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ ከሌሎች ከተሞች ይበልጥ ብዙ ተአምራት ያደረገባቸውን ከተሞች፥ ንስሓ ስላልገቡ እንዲህ ሲል ይወቅሳቸው ጀመር፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ የሚበዙ ተአምራት የተደረገባቸውን ከተማዎች ንስሐ ስላልገቡ ሊነቅፋቸው ጀመረ እንዲህም አለ፦ |
እኔ በጥንቃቄ አደመጥኋቸው፤ ትክክለኛ የሆነውን ግን አይናገሩም። ማንም ስለ ክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ “ምን አድርጌአለሁ?” ይላል። ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ፈረስ፣ እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይሄዳል።
የነነዌ ሰዎች በፍርድ ዕለት ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ እነርሱ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና። እነሆ፤ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።
ከዚያም ዐሥራ አንዱ በማእድ ላይ ሳሉ ተገለጠላቸው፤ ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች የነገሯቸውን ስላላመኗቸው፣ አለማመናቸውንና የልባቸውን ድንዳኔ ነቀፈ።
ኢየሱስም መልሶ፣ “የማታምን ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጁን ወደ እኔ አምጡት።” አላቸው።
ዳግመኛም ስመጣ አምላኬ በእናንተ ፊት ያዋርደኝ ይሆን ብዬ እፈራለሁ፤ ይኸውም ብዙዎች ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኀጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፣ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን ነው።
እነርሱም በታላቅ ሐሩር ተቃጠሉ፤ በእነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ እንጂ ንስሓ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም።