ማቴዎስ 11:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ተብሎ የተጻፈለት እርሱ ነው፤ “ ‘መንገድህን በፊትህ የሚያዘጋጅ፣ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤” ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ‘እነሆ፥ እፊት እፊትህ እየሄደ፥ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ በፊት እልካለሁ’ ተብሎ የተጻፈለት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ |
“እነሆ፤ በፊቴ መንገድ የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ ደስ የምትሰኙበትም የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ይመጣል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እውነት እላችኋለሁ፤ ከሴት ከተወለዱት መካከል እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ አልተነሣም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።
በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረለት እርሱ ነው፤ “በምድረ በዳ፣ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጐዳናውንም አስተካክሉ’ እያለ የሚጮኽ ድምፅ።”