ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣ የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ! ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል።
ማቴዎስ 10:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ የመጣሁት ሰላምን በምድር ለማስፈን አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማውረድ አልመጣሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የመጣሁት፥ ሰላምን በምድር ላይ ለማምጣት አይምሰላችሁ፤ እኔ ጦርነትን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። |
ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣ የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ! ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል።
ሌላ ፍም የሚመስል ቀይ ፈረስም ወጣ፤ ተቀምጦበት የነበረው ሰላምን ከምድር ላይ እንዲወስድና ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ለማድረግ ሥልጣን ተሰጠው፤ ትልቅም ሰይፍ ተሰጠው።