እንዲሁም የልብሴን ዘርፍ አራግፌ፣ “ይህን የተስፋ ቃል የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው አምላክ ቤቱንና ንብረቱን እንደዚህ ያራግፈው፤ እንደዚህ ያለውም ሰው ይርገፍ፤ ባዶም ይሁን” አልሁ። በዚህም ጉባኤው ሁሉ፣ “አሜን” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም የገቡትን ቃል ፈጸሙ።
ማቴዎስ 10:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም ሰው ሊያስተናግዳችሁ ወይም የምትናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ከቤቱ ወይም ከከተማው ስትወጡ የእግሮቻችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም የማይቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የማይሰማ ከሆነ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉችሁ ውጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው የማይቀበላችሁ ወይም ቃላችሁን የማይሰማ ቢሆን ያንን ቤት ወይም ከተማ ለቃችሁ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። |
እንዲሁም የልብሴን ዘርፍ አራግፌ፣ “ይህን የተስፋ ቃል የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው አምላክ ቤቱንና ንብረቱን እንደዚህ ያራግፈው፤ እንደዚህ ያለውም ሰው ይርገፍ፤ ባዶም ይሁን” አልሁ። በዚህም ጉባኤው ሁሉ፣ “አሜን” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም የገቡትን ቃል ፈጸሙ።
የትኛውም ቦታ የማይቀበላችሁ ወይም የማይሰማችሁ ከሆነ፣ ከዚያ ስፍራ ስትወጡ ምስክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን ትቢያ በዚያ አራግፋችሁ ውጡ።”
“ከእነዚህ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበለኝ ማንም ቢኖር የሚቀበለው እኔን ሳይሆን የላከኝን ነው” አላቸው።
እንዲህም አላቸው፤ “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ማንም ቢኖር እኔን ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ደግሞ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ከሁሉ ይበልጣልና።”
ነገር ግን በተቃወሙትና በሰደቡት ጊዜ ልብሱን አራግፎ፣ “ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን! እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከእንግዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ” አላቸው።