ከዚያም እንዲህ አለ፤ “ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ ተናግሮ የሰጠውን ተስፋ፣ እርሱ ራሱ በእጁ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበርና፤
ማቴዎስ 1:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሁሉ የሆነው ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው እንዲፈጸም ነው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ የሆነው ጌታ እንዲህ ሲል በነቢይ አማካይነት የተናገረው እንዲፈጸም ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነቢይ ከጌታ ዘንድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነቢይ ከጌታ ዘንድ፥ |
ከዚያም እንዲህ አለ፤ “ለአባቴ ለዳዊት በገዛ አፉ ተናግሮ የሰጠውን ተስፋ፣ እርሱ ራሱ በእጁ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበርና፤
በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያ ዓመት፣ በኤርምያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በግዛቱ ሁሉ ዐዋጅ እንዲያስነግርና ይህም እንዲጻፍ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤
በዚያም ሄሮድስ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ኖረ። በዚህም፣ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት” በማለት ጌታ በነቢዩ አንደበት የተናገረው ቃል ተፈጸመ።
እርሱም፣ “ከእናንተ ጋራ በነበርሁበት ጊዜ፣ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል’ ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው” አላቸው።
እኔ ከእነርሱ ጋራ ሳለሁ፣ በሰጠኸኝ ስም ከለልኋቸው፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ከአንዱ ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ ዕቅዱን እንዲፈጽሙ፣ ደግሞም በአንድ ሐሳብ እንዲስማሙና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው እንዲሰጡ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነውና።