ማቴዎስ 1:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ እንዲህ ነው፤ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳይገናኙ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንዲህ ነበር፤ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳለች ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ሁኔታ እንዲህ ነበር፦ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳለች፥ ሳይገናኙ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። |
ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት።
እንግዲህ ለእኛ የሚያስፈልገን፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ንጹሕ፣ ከኀጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ የከበረ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው።