ማርቆስ 5:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኞቹ ሸሽተው ሄዱ፤ ወሬውን በከተማና በገጠር አዳረሱት፤ ሕዝቡም የሆነውን ለማየት ካለበት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እረኞቹ ሸሽተው ሄዱ፤ በከተማና በገጠርም አወሩ፤ ሕዝቡም የሆነውን ለማየት መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐሣማዎቹ እረኞች ሸሽተው ሄዱ፤ በከተማና በገጠር ወሬውን አወሩ፤ ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ከየቤታቸው ወጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩ፤ ነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩ፤ ነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ። |
እርሱም ፈቀደላቸው። ርኩሳን መናፍስቱም ወጥተው በዐሣማዎቹ ገቡባቸው፤ ሁለት ሺሕ ያህል ዐሣማዎችም በገደሉ አፋፍ በመንደርደር ቍልቍል ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጠሙ።
ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ፣ የአጋንንት ሰራዊት ሌጌዎን ዐድረውበት የነበረው ሰው፣ ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት በዚያ ተቀምጦ አዩት፤ ፈሩም።